መንገዱ (ጸሎት)  The Path (Prayer)

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

ከኋላህም ሆኖ የሚናገርህን ድምጽ ትሰማለህ፥ እንዲህ ሲል ‘’መንገዱ ይህ ነው፡ በእርሱ ሂድ’’። ይህ ድምጽ በቤቶቻችንና በትዳሮቻችን ውስጥ ይሁን። ሁሉም ወንዶች ይህንን ድምጽ እንዲሰሙ እፈልጋለሁ። ድምጹ ከኋላህ ሆኖ ‘’መንገዱ ይህ ነው በእርሱ ሂድ’’ እያለ ይመራሃል።

ወደ አንተ ለመምጣት በማልፍባቸው መታጠፊያዎችና አቅጣጫ ፍለጋዎች ይህንን ድምጽ በሕይወቴ እንድሰማ አድርገኝ። ሰው ሁሉ ምሪት በማይኖረው ጊዜ ‘’መንገዱ ይህ ነው በእርሱ ሂድ’’ የሚለውን ድምጽ እንድሰማ አድርገኝ። እኛ የእግዚአብሔርን ድምጽ በግልጽ እንሰማለን። በብርሃን ወቅት በትክክልና በግልጽ እንሰማለን። ስለዚህ እንዲህ እንላለን፥ እግዚአብሔር ሆይ ድምጽህ በልቦቻችን ውስጥ የበለጠ ግልጽና የጠራ ይሁን። የእግዚአብሔር በሆነውና የእግዚአብሔር ባልሆነው መካከል፥ ጽድቅ በሆነውና በእርኩሱና ባልተቀደሰው መካከል፥ እውነት በሆነውና ሐሰት በሆነው መካከል በግልጽና በጥንካሬ መለየት የሚያስችለንን ኃይል ስጠን። ከኋላችን ሆኖ ‘’መንገዱ ይህ ነው በእርሱ ሂድ’’ የሚለውን ድምጽ እንድንሰማ አድርገን።

ከሰማያት አቅጣጫ ጠቋሚና ከፍ ካለው የስልጣን ስፍራ ግልጽ መለኮታዊ ምሪትን ስጠን። ከዚህ ፕላኔት ግራ መጋባት በላይ ከፍ ካለው ስፍራ፣ ከውሸቶቹና ከፍልስፍናው በላይ ከፍ ካለው ስፍራ፣ ካለመንጻትና ከእርኩሰት በላይ ከፍ ካለው ስፍራ ‘’መንገዱ ይህ ነው በእርሱ ሂድ’’ የሚለውን ድምጽ እንድንሰማ አድርገን። ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘመን መጨረሻ ድረስ፣ በታላቁ ኃይልህና በጽኑ ብርታትህ በምድር ላይ በምታመጣቸው በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ ይህንን እንድንሰማ አድርገን። በዚህ ሁሉ ውስጥ ወደ አንተ ዙፋን የሚያደርሰንን ብሩህ መንገድ አዘጋጅልን።

‘’መንገዱ ይህ ነው በእርሱ ሂድ በእርሱ ሂድ በእርሱ ሂድ’’ የሚለውን ድምጽ በልቦቻችን ውስጥ እየሰማን እያለን እግሮቻችንን በዚህ መንገድ ላይ እንድናስቀምጥ እምነት ስጠን።