ለዘለዓለም  Forever

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

[ቁ.1]

ጉልበቴ ነህ
ጽኑ ጋሻዬ
መመኪያዬ
እምነቴ በአንተ ላይ ነው
የነፍሴ ደስታ መሸሸጊያዬ

[አዝ.1]

ለዘላለም ከፍ በል – ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ከፍ በል ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ

[ቁ.2]

እውነቴ አንተ ነህ
መሪዬም ነህ
ሁሉን ቻይ ጌታ
ነፍሴ የምትወድህ
እወድስሃለሁ አከብርሃለሁ

[አዝ.2]

አገንሃለሁ – ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ከፍ በል ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ

[ጸሎት]

‘’የምናደርጋቸው ብዙዎቹ ነገሮች ወደፊት ይቆማሉ። አምልኮአችን ግን ለዘለዓለም ይቀጥላል። አሜን? እኛ ግን ለዘለዓለም እርሱን እናመልከዋለን። እርሱን በምናመልክበት ጊዜ ዘለዓለማዊውን ባህርይ እንለማመዳለን። አእምሮአችንን የያዙት ነገሮች ሁሉ ጸጥ ይላሉ። አምልኮአችን ግን ለዘለዓለም ይቀጥላል። አሜን? ሁልጊዜ ልቦቻችንን ለዘለዓለም ወደ እርሱ ከፍ እናደርጋለን። እግዚአብሔርን በምታመልኩበት ጊዜ፥ ‘’ምድርን እክዳለሁ ጊዜን እክዳለሁ ሞትን እክዳለሁ ሟችነትን እክዳለሁ በሰብአዊ ልምምዴ ውስጥ ዘለዓለማዊ የሆኑ ነገሮች አሉ እያላችሁ እያወጃችሁ ነው። ስለዚህ አምልኮአችን ለዘለዓለም ይቀጥላል!’’

[አዝ.3]

ለዘላለም ከፍ በል – ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ከፍ በል ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ

[አዝ.4]

አገንሃለሁ – ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ከፍ በል ጌታ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ