ላከን (ጸሎት)  Send Us (Prayer)

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

አንተ የእኔ ሰንበት ነህ። አንተ የእኔ እረፍት ነህ። አንተ የጉዞዬ መጨረሻ ነህ። ስለዚህ ኃይልንና ጥንካሬን ስጠን። በዚህ ጊዜ የምንጠይቅህ ነገር ቢኖር እንድትልከን ነው፤ ላከን ላከን።

ይህ የእረፍት ጊዜ አይደለም ላከን። ይህ የኃይል ቀን ነው ላከን። እግዚአብሔር ሆይ የምንጠይቅህ ነገር ቢኖር እንድትልከን ነው። እረፍት አንጠይቅህም እረፍት የሚመጣው አንተ ተመልሰህ ስትመጣ ነው። ወደ አንተ የምናሰማው ጩኸት ፈቃድህን ለማድረግ እንድትልከን ነው፤ ላከን።

ወደፊት ላከን በአዲስ መንገድ ወደፊት ላከን። እንደ አንድ ሕዝብ ወደፊት ላከን። በእኩልነት ወደፊት ላከን። ለመጪው ዘመን በመዘጋጀት ወደፊት ላከን። በብርሃንና በመረዳት፣ በእውቀትና በጥንካሬ ወደፊት ላከን። በትክክለኝነት ወደፊት ላከን። በቅድስናና ለእግዚአብሔር በመለየት ወደፊት ላከን፥ በልብ ንጽሕና ወደፊት ላከን።

ያለ ምንም ኃጢአትና ከመንገድ ባለመውጣት ወደፊት ላከን። ንጹህና ቅዱስ በመሆን ወደፊት ላከን። ኦ ላከን ወደፊት ላከን። በታላቅ ብርታትህ ወደ መጪው ዘመን አንቀሳቅሰን።

በዚህ ስፍራ ያሉትን የእያንዳንዱን ወንድና ሴት ልብ አዘጋጅ። ልቦቻችንን በሰላም አስታጥቅ። በደስታ ወደፊት ላከን። ስራው ወደ መፈጸም ይምጣና እርካታን ይፍጠር። ታላቁ ስራ በልቦቻችን ውስጥ እርካታንና አንተን መፈለግን ይፍጠር። እኛ የምንለምንህ ነገሮች እነዚህ ናቸው። የልቦቻችን ጩኸቶች እነዚህ ናቸው። ወደ አንተ የምናቀርባቸው አስፈላጊ ነገሮች እነዚህ ናቸው።

የጸሎቶቻችንን ድምጽ አድምጥ። የሕዝብህን ጩኸት አድምጥ።

በጌታችን ምሳሌዎች መሰረት እንደ ፈቃድህ እንጸልያለን።

ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ። ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ። ተመስገን ጌታ ሆይ። ተመስገን ኢየሱስ። ለዘለዓለም