ስምህ ይመስገን (ጸሎት)  We Praise Your Name (Prayer)

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

ኦ አባት ሆይ ዛሬም እንባርክሃለን፤ እናከብርሃለን። እንደ አንተ ያለ አምላክ ማንም የለም። እንደ አንተ ያለ አዳኝ ማንም የለም፤ እንደ አንተ የሚቤዥ ማንም የለም። እንደ አንተ ያለ ንጉሥ የለም። እንደ አንተ ያለ ጌታ የለም። በተስፋ፣ በደስታ፣ በአድናቆትና በአምልኮ ወደ አንተ እመለከታለሁ። እኔ አመልክሃለሁ።

ክብርን እሰጥሃለሁ። ከፍ አደርግሃለሁ። አገንሃለሁ፤ አንተ የተገባህ ነህና። አንተ ብቻህን ምስጋናዬን ልትቀበል የተገባህ ነህ። አምልኮዬን ለአንተ እሰዋለሁ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ፣ ንጉሤ፣ ጌታዬ፣ አምላኬና አዳኜ እባርክሃለሁ። በእኔ ውስጥ ያለ ማንኛውም ነገር የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።