ቅዱስ ቅዱስ  Holy, Holy

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

[አዝ]

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህ እግዚአብሔር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህ እግዚአብሔር

[ቁ.1]

ጌታ ሆይ በፊትህ እንቆማለን
በኃይልህና ብርታትህ የሰራኸን ሕዝብህ
እጆቻችንን አንስተን ወደ ገዢው ንጉሥ
ከዘለዓለም እስከ ዘዓለም

[ቁ.2]

ያንተን ዘር በእኛ ውስጥ አስቀምጠሃል
ክቡር ስጦታህን እንጠብቀዋለን
አንተን መፍራት ይኖራል በውስጣችን
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም

[ጸሎት]

እባርክሃለሁ። ቅዱሱን ስብእናህን እባርከዋለሁ። ቅዱሱን ስምህን እባርከዋለሁ። በምድር ላይ ድምጼን ከፍ አድርጌ እባርክሃለሁ። ከጊዜ ወሰን ውስጥ ወደ ዘለዓለማዊነት ውስጥ ገብቼ እባርክሃለሁ። በሟችነት ውስጥ ድምጼን ከፍ አድርጌ ዘለዓለማዊ ህልውናህን እባርካለሁ። መልካምነትህን እባርካለሁ።

ኦ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ በውስጤ ያለ ነገር ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኩ።