አመልክሃለሁ (ጸሎት)  I Worship You (Prayer)

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

“እኔ አመልክሃለሁ”
እነዚህ ቅዱስ ቃሎች ለእርሱ ብቻ የተለዩ ናቸው፤ ለእርሱና ለእርሱ ብቻ።

“እኔ አመልክሃለሁ”

እኔ አከብርሃለሁ። እኔ ከፍ አደርግሃለሁ እወድስሃለሁ። አምልኮዬን ልትቀበል የሚገባህ አንተ ብቻ ነህ። አንተ ምስጋናዬን ልትቀበል የተገባህ ነህ።

እኔ አከብርሃለሁ። እኔ አመልክሃለሁ። እኔ እባርክሃለሁ። ዛሬም ለዘላለም ከንፈሮቼ ያመስግኑህ። ነፍሴ ዛሬም ለዘላለም ትባርክህ። ኦ አምላኬ ሆይ ምስጋናዬን ሁሉ ልትቀበል የሚገባህ አንተ ብቻ ነህ።

ይህንን ቃል የምሰጠው ምንም ዓይነት ፍጥረት፣ ምንም ዓይነት ነገር የለም፥ “እኔ አመልክሃለሁ”።
በጊዜ ውስጥም ሆነ በዘላለማዊነት ውስጥ ይህንን ሊቀበል የሚገባው ማንም የለም፤ ምንም ነገር የለም። እነዚህ ቃላቶች ለአንተና ለአንተ ብቻ የተለዩ ናቸው። “እኔ አመልክሃለሁ” ዘላለማዊ አምላክ።

እኔ አመልክሃለሁ ሁሉን ቻይ አምላክ፣ በሰማያት ያለኸው ታላቅ ንጉሥ እኔ አመልክሃለሁ። ፈጣሪዬ፣ አዳኜና አምላኬ። እኔ አመልክሃለሁ።

“እኔ አመልክሃለሁ”