እናመልክሃለን  We Worship You

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

[ጸሎት]

እናመልክሃለን እንባርክሃለን፣ ስምህን እናገነዋለን። ልክ እንደ አባቶቻችን እጆቻችንን ወደ አንተ እናነሳለን፥ በቀድሞ ዘመን የነበሩት አባቶቻችን የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ሉአላዊው አምላክ ያነሱ እንደነበር፥ ልክ ወንድሜ ዕንባቆም ከረጅም ዓመታት ዓመታት በፊት

‘’እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል። ሐሴትም አደርጋለሁ አንተ ሉአላዊው አምላክ ኃይሌ ነህ።’’ ብሎ እንደተናገረ፥ አንተ የወንድሜ ጥንካሬ ነህ። ‘’አንተ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች አድርገሃቸዋል። አጠንክረኸኛል፥ በከፍታዎችም ላይ ታስኬደኛለህ።’’

እኛም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ወደፊት በመቅረብ ዓይኖቻችንን ቀና አድርገን ተነስተን በአንተ ክብር ውስጥ እንራመዳለን፥ ቅዱስ ስምህን እንባርከዋለን።

ስለ ቃልህ እናመሰግንሃለን። ስላሰለጠንከን እናመሰግንሃለን። ስላስተማርከን እናመሰግንሃለን። የእግዚአብሔር ቃል በልቦቻችን መልካም መሬት ላይ ይውደቅ፥ በጥልቀት ስር በመስደድ የእግዚአብሔር ነገሮችን በወንድሞቼ ውስጥ በመላው ቅዱሳኖችህ ውስጥ ሰላሳ እጥፍ፣ ስልሳ እጥፍና፣ መቶ እጥፍ ያፍሩ።

ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ። እንባርክሃለን። አሜን። አሜን።

[አዝ]

እንባርክሃለን
ክብርን እንሰጥሃለን
ገናና ነህ ለዘለዓለም

ሉአላዊ አምላካችን
ኃይላችን ነህ
እናመልክሃለን ዘለዓለም