እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ (ጸሎት)  I Lift My Hands To You (Prayer)

Artist: Congress MusicFactory
Produced By: Congress MusicFactory
Album: አማርኛ  We Worship You

እስቲ የተቀደሱ እጆቻችንን ወደ ጌታ እናንሳ። አሜን? አባት ሆይ ሁላችንም እያንዳንዳችን እጆቻችንን ወደ አንተ እናነሳለን። በአጠገቤ ያለው ወንድሜ እጆቹን ወደላይ አንስቷል፣ በአጠገቤ ያለችው እህቴ እጆቿን ወደላይ አንስታለች። ይህንን የውበት የቅንነትና የመታዘዝ ረጅም መስመር አስባለሁ። ወደዚህ ስፍራ ያመጣንን የመታዘዝ ውበት አስባለሁ። እጆቼን ወደላይ አንስቼ ከፊታችን ቀድመው የሄዱትን የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን መስዋዕትነት አስባለሁ፤ የጠላትን ተግዳሮት በመጋፈጥ ዛሬ እኛ የምንራመድበትን የብርሃን መንገድ እንዲፈጠር ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡትንና ደማቸውን ያፈሰሱትን ሁሉ አስባለሁ። እጆቼን ወደላይ ሳነሳ እነርሱን አስታውሳለሁ። አሁን የሆንኩትን እንድሆን የሰራኝንና የቀረጸኝን አስታውሳለሁ። እነዚያ ቃላቶች ጩኸቶች ቆራጥነት መስዋዕትነትና መታዘዝን አስባለሁ። ከዓመታት ወደ ዓመታት ከትውልድ ወደ ትውልድ፤ እኛ ዛሬ የቆምንበትን ይህንን አውራ ጎዳና የፈጠሩትን እነዚያን መስዋዕቶች አስባለሁ።

ስለ አንተ በምስጋና ተሞልቻለሁ፣ ስለ ጽናትህ ስለ ታማኝነትህ። ለመገንባት ስላለህ ቆራጥነት ስለ ፍሰትህ ስለ ማበረታታትህና መንፈስህን በሰዎች ልብ ውስጥ ስለ መላክህ በምስጋና ተሞልተናል። የማመሰግንበት ምክንያት አንተ ሕይወት ስለ ሰጠህን ነው። የማመሰግንበት ምክንያት ልባችን ለመዘመር ስለተነሳ ነው። የማመሰግንበት ምክንያት በወንድሞቼ መካከል ተቀምጬ፥ የአንተ ብርሃን ወደ አእምሮዬ ወደ ነፍሴና ወደ መንፈሴ ስለመጣ ነው። የመሪዎቼን ድምጽ መስማቴ የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ መስማቴና የእግዚአብሔርን ፊት መመልከቴ እጅግ ጥልቅ ክቡርና ውብ ነገር ነው። አንተን በማየቴ የተሻለ ወንድ አድርጎኛል። አንተን በማየቴ አባት ሆይ፥ ወደ ልብህ በመቃኘቴ የተሻለ ወንድ አድርጎኛል፥ የተሻለ ሰው አድርጎኛል፥ ስለዚህ በምስጋና ተሞልቻለሁ።

ስለ ጠበቅኸኝ አመሰግንሃለሁ፣ ስለ መራኸኝ አመሰግንሃለሁ፣ እጅህን በእኔ ላይ ስላደረግህ አመሰግንሃለሁ። ሕይወት ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፣ እኔን ለማሰልጠን ስለ ታገስክ አመሰግንሃለሁ። ከሞኝነት አውጥተህ ወደ ጥበብ ስለመራኸኝ አመሰግንሃለሁ። ከድካም አውጥተህ ወደ ጥንካሬ ስለ መራኸኝ አመሰግንሃለሁ። ጥርጥርን ከውስጤ አውጥተህ እምነት ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ከሞት አውጥተህ የተትረፈረፈ ሕይወት ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ከብቸኝነት አውጥተህ በዚህ ፍጹም አስደናቂ በሆነ ሕዝብ መካከል ስላስቀመጥከኝ አመሰግንሃለሁ። ከመባዘን አውጥተህ ጉዞ ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። በምስጋና ተሞልቻለሁ። ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ! ተመስገን ጌታ ሆይ! ስለ ፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ። ሕይወት ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ስለ ሾምከኝ አመሰግንሃለሁ። ተልእኮ ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ስለ መረጥከኝ አመሰግንሃለሁ። ስለ መራኸኝ አመሰግንሃለሁ። አመሰግንሃለሁ! አመሰግንሃለሁ! አመሰግንሃለሁ! አመሰግንሃለሁ! ስለ እያንዳንዱ ውጊያ አመሰግንሃለሁ። ስለ እያንዳንዱ ድል አመሰግንሃለሁ፣ ስለ እያንዳንዱ ፈተና አመሰግንሃለሁ። አስቸጋሪ ስለሆነው ስፍራ አመሰግንሃለሁ። ቀላል ስለሆነው ስፍራም አመሰግንሃለሁ። ስለ ሁሉም ነገር፣ ስለ እያንዳንዱ ጊዜና ስለ እያንዳንዱ ቀናት፣ ታላቁ እጅህ ሕይወቴን ስለነካበት ስለ እያንዳንዱ ስፍራ አመሰግንሃለሁ። ተመስገን እልሃለሁ! ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ! አመሰግንሃለሁ።